አያመጣው የለ መስከረምና ጥቅምት፤ ተሰቃየች ነፍሴ በኢሬቻ ቅናት። Amhara and Pseudo Amhara Elites' Tribulation with the Beauty of Irreechaa Celebration

መስከረምና ጥቅምት፣ የኢሬቻ ቅናት
ኦሮሞዎች በየአመቱ ፈጣሪያቸዉን ለማመስገን ሽር ጉድ ብለው አምሮባቸው ሲወጡ ፤ በቅናት ላይ የተመሰርተ አዲስ የጎንዮሽ ሰይጣናዊ ጋጋታ ባለፉት አመታት መከሰቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህም ቅናታዊ፤ "አፀያፊ ልምድ" ወይም "የኢሬቻ ቅናት" እንበለው፤ ኦሮሞን መሳደብ፤ባህሉን ማንቇሸሽና ከሀይማኖት ጋር አስታከው የሌለ ትርክት መፍጠርን ያካትታል።
በዉነቱ ችግራቸው አይገባንም። ጫጫታው ኦሮሞን ለማዳን ይሆን? አይመስልም። ኦሮሞ ሲኦል እንዳይገባ ሊያድኑት ይሆን? ይህም አይመስልም፤ ቢሆንማ አይተው እንዳላዩ ዝም ይሉ ነበር።
አዉራዎቹ ዘንድሮ የት ጠፉ?
በየአመቱ በኢሬቻ ጥላቻ የታወቁቱ አዉራዎች—እንደ ሃብታሙ እና ዘመድኩን ያሉ —ብቅ በለማለታቸው ምን ሆነው ነው ብለን ሃሳብ ገብቶን ነበር። ሰለቻቸው? ለኢሬቻ እጅ ሰጡ ወይ? ከኢሬቻ አክባሪዎች ጋር ተቀላቀሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመርን።
ግን ሳይዉል ሳያድር አዲስ መረጃ ከተፍ አለ። ይህም በ"ትብብር (ፅምዶ)" ፕሮፓጋንዳ ተጠምደው እንደተለመደው ኢሬቻን ለማንቇሸሽ ጊዜ ማግኘት አልቻሉም የሚል። ቢሆንም ብዙ ግልገሎችና ሥራፈት ፓስተሮች፤ ቄሶች፤ ወዘተ እንደተሰማሩ [1] ተረድተናል።
ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ እስከ ዛሬ ድረስ የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ ግልፅ አይደለም። ምንድነው የሚፈልጉት? ኦሮሞ ኢሬቻን ይተው ነው? ይህ የማይቻል የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው። አልፎ ተርፎ ወሰን የሌለው "የእኔ አዉቅልሀለሁ እብሪት" ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ምክር ለግሱኝ ብሎ አያውቅም፤ የሚያደርገዉንም ያዉቃል። ከንቱ ጩኸት ነው።

እሬቻ፣ በእዉነቱ ምንድነው?
እሬቻ የምስጋና በአል እንጂ ሀይማኖት አይደለም። አዎን፤ ከዋቄፋና ሀይማኖት ጋር መያያዙ ታሪካዊ ሀቅ ሲሆን፣ የገና በአል ከክርስትና ሀይማኖት ጋር ተያይዞ እራሱ ግን ሀይማኖት እንዳልሆነ፤ የመዉልድ በአል ከእስልምና ሀይማኖት ጋር ተያይዞ እራሱ ግን ሀይማኖት እንዳልሆነ ማለት ነው። ሀይማኖት እኮ አንዴ ብቻ በአመት አይከበርም። ሀይማኖት በየቀኑ በየደቂቃዉ ከኛ ጋር ያለ አምልኮ ነው ማለት ይቻላል።
የአሜሪካው Thanksgiving በአል ከ"እርሻ ምርት" ምስጋና ጋር እንደመያያዙ መጠን እንዲሁ የፀደዩ ኢሬቻ ከክረምት ጭለማ ወደ ፀደይ ብርሃን መሸጋገርን ያከብራል። እንደኢሬቻ ሁሉ Thanksgiving የሀይማኖት ሀረግ አለው። ከዚያም አልፎ የሰው ልጅን ዉጣዉረድ — ድርቀት፣ በሽታ፣ ጦርነት፣ ፖከቲካ — የመሳሰሉት ተካተው እጅግ ተወዳጅ በአል በመሆን አድጏል፣ ፀንቷል።
የፀደይ ኢሬቻን ካነሳን ዘንድ፣ የበልግ ኢሬቻ — Ireechaa Afraasaa, Autumn Irreechaa — መኖሩን ያስታዉሰናል። እንደፀደይ ኢሬቻ በአሁኑ ጊዜ በድምቀት ባይከበርም፣ የበልግ ኢሬቻ ተራራ ላይ በመዉጣት ዝናብ እንድዘንብ ፈጣሪን የመማፀን በአል ነው። በዱሮ ጊዜ ቱሉ ጩቃላ የበልግ ኢሬቻ ማእከል በመሆን ሕዝብ ያሰባስብ እንደነበር ታሪክ ያስታዉሰናል።
በመጨረሻም ...
እንድትገነዘቡ የምንወደው ነገር ቢኖር ስድባችሁን እንድታቆሙ ነው። ከዚህም አልፎ እሬቻ የሰላምና የፍቅር በአል እንደመሆኑ ከእኛ ጋር ብታከብሩ ደስታ ይሰማናል። ይህንን ከልክ ያለፈ የመስከረም እና ጥቅምት መጥፎ ልምድ እርግፍ አድርጋችሁት ተዉት። የኦሮሞ ህዝብ ያዝንባችሗል። የሚስቁባችሁም ብዙ ናቸው። ለሰላምና ለመከባበር ትጉ።
እስቲ መጪዉን የ2020 የመስከረምና ጥቅምት ወራት የቅናት ሳይሆን የቀና መንገድ ወራት ለማድረግ ጥረት አድርጉ። ፈጣሪ ይርዳችሁ።
Those who came from thousands of miles away saw thanksgiving, peace, beauty and belonging [2]. Some who live together and next door apparently saw something to fear [3].
References
- የደም ግብር በኢሬቻ!! ብፁዕ አባታችን በቁጣ መልዕክት አስተላለፉ / ጳጳሱ ምን ነካው / በሕዝብ ፊት ተዋረደ, 3 October 2026, ክብረ ተዋሕዶ ሚዲያ YouTube Channel, YouTube.
- Tuuristoota Ayyaana Irreechaarratti hirmaachuun jajan, 3 October 2026, OBN Oromiyaa YouTube Channel, YouTube.
- OT Editorial, Much Ado About Irreechaa: Psychology Behind the Criticism of Oromo Thanksgiving, 30 September 2025, OROMIA TODAY.






